❶. አፕሊኬሽኑን ከገዛሁ በኋላ ለምን ያህል ጊዜ ያገለግላል?
መልስ: አፕሊኬሽኑን ከገዙት በኋላ ስልክ እስካልቀየሩ ድረስ እስከ ዘለዓለም ይሰራል ። ስልክ ከቀየሩ ደግም ተራ ቁጥር 2 ላይ የተጻፈውን ዕድል መጠቀም ይችላሉ ።
❷. አፕሊኬሽን ከገዛሁ በኋላ ስልክ ብቀይር ወይም ስልኬ ቢጠፋ ድጋሜ መክፍል አለብኝ?
መልስ፦ በፍጹም። አንድ አፕሊኬሽን ከገዙ በኋላ ስልክዎ ቢጠፋ ወይም ቢቀይሩ እስከ ሁለት ዙር ድረስ በነፃ ኮድ መጠየቅ ይችላሉ። ከሁለት ጊዜ በላይ ግን መጠየቅ አይችሉም። ይህም በጠፋብኝ ሰበብ በዙ ኮድ በመጠየቅ የሚያጭበረብሩ ሰዎችን ለመቆጣጠር ነው። አንድ ሰው ስልክ ቢቀይር የመክፈቻ ኮድ በነፃ መጠየቅ የሚችለው የመጀመርያውን ኮድ ካገኘበት ቀን በኋላ ቢያንስ 30 ቀናት ፣ የሁለተኛውን መክፈቻ ኮድ ካገኘበት ቀን በኋላ ደግሞ 90 ቀናትን መቆየት አለበት።
❸. አፕሊኬሽን ከገዛሁ በኋላ የተጠቀሱትን የመጻሕፍት ዝርዝር ይዞ ባይገኝ የከፈልኩት ብር ተመላሽ ይሆናል?
መልስ፦ የገዙት አፕሊኬሽን እንደጠበቁት ሆኖ ባያገኙት ወይም የተጠቀሱትን የመጻሕፍት ዝርዝር ይዞ ባይገኝ የከፈሉት ብር ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተመላሽ ይሆናል። ይህም ከከፈሉበት ቀን ጀምሮ ባሉት ፴ (ሠላሳ) ቀናት ብቻ ነው። የገዙት አፕሊኬሽን ሠላሳ ቀን ካለፈው የይመለስልኝ ጥያቄ ማቅርብ አይችሉም።
❹. ክፍያው ምን ያህል አስተማማኝ ነው?
መልስ፦ ክፍያው ሙሉ በሙሉ በባንክ ብቻ የሚፈጸም በመሆኑ ለከፈሉት ብር ሙሉ የሕግ ደጋፍና ዋስትና ይኖርዎታል። ነገር ግን በተሳሳተ መረጃ ተጭበርብረው የከፈሉት፣ በተሳሳተ መረጃ የተወሰደብዎት ብር ካለ የከፈሉበትን የባንክ ደረሰኝና የተጠቀሱትን አድራሻዎች በመጠቀም የሕግ አካላትን ማማከር ይችላሉ።
❺. አፕሊኬሽኑን አፕዴት ሳደርገው ክፍያ ይጠይቃል?
መልስ: በፍጹም ። አፕሊኬሽኖችን በየጊዜው ስለምናዘምናቸው ያለምንም ክፍያ Update ማድረግ ይችላሉ።
❻. ከአንድ በላይ ሆኖ መግዛት ወይም ለሌላ ሰው መግዛት ይችላል?
መልስ: ይቻላል ። በተለይ ከኢትዮጵያዊ ውጪ የምትኖሩ በማኅበር ወይም በቡድን በአንድ ሰው ስም መግዛት ትችላላችሁ ። ከዚያም የመክፈቻ ኮድ ለእያንዳንዳችሁ ይላክላችኋል ።
❼. ቅናሽ የሚደረገው መቼ ነው?
መልስ: አንድ ሰው ከሦስት አፕሊኬሽኖች በላይ ሲገዛ የ20% ቅናሽ እናደርጋለን ። በቡድን ደግሞ ከ6 በላይ አፕሊኬሽኖችን ለሚገዙ የ35% ቅናሽ እናደርጋለን ።
0 Comments