አብነት ዘተዋሕዶ Abinet Zetewahido



የአብነት ትምህርት ቤት መግባት ላልቻሉ ቀዳሚ አማራጭ የመማርያ መተግበርያ ነው፡፡
ይህ መተግበርያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የአብነት የቃል ትምህርት በድምጽና በጽሑፍ አቀናጅቶ እጅግ ለአጠቃቀም ምቹ ሆኖ የቀረበ መተግበሪያ ነው፡፡ መተግበርያው ያለምንም መምህር እርዳታ የግዕዝ የጸሎት ምንባባትን በጽሑፍና በድምጽ እንዲማሩ ያስችልዎታል፡፡

መተግበርያውን ልዩ የሚያደርገው
  • መተግበርያውን ልዩ የሚያደርገው
  • ድምጹ የሚያነበው ቃልና በጽሑፍ ያለው ቃል አብሮ እንዲሄድ ስለተሰራ የሚነበበው ቃል በራሱ ጊዜ እየቀለመ ከድምጹ እኩል አብሮ መሄድ ይችላል፡፡
  • የሚፈልጉትን ዐረፍተ ነገር ወደፊትና ወደ ኋላ እያሳለፉ እንዲያነብልዎት ማድረግ ያስችልዎታል፡፡
  • ገጾችን ያለምንም ሰው እርዳታ ወደ ላይና ወደታች እንዲሁም ወደሚቀጥለው ገጽ ማዞር ይችላል፡፡
  • የአብነት ትምህርትን በቀላሉ መማር ይችላሉ፡፡
  • መተግበሪያውን በአማርኛ በእንግሊዝኛ ተርጉመው መጠቀም ይችላሉ፡፡
  • የፈደል መጠኑን በሚፈልጉት መጠን ማሳደግና ማሳነስ ይችላሉ፡፡
  • በቀንና በሌሊት እንዲሁም በብራና ቀለም በእርስዎ ምርጫ የመጽሐፉን ገጽታ መቀየር ይችላሉ፡፡
  • የሚፈልጉትን የጸሎት ክፍል በቀላል መፈለግ ያስችልዎታል፡፡
  • ያለድምጽ ለመጸለይ ካሰቡ ድምጹን ማጥፋት ይችላል፡፡

1 Comments