መተግበሪያዎችን ከጎራንዳ ሲስተም እንዴት መግዛት እንችላለሁ፡፡ (ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚኖሩ ብቻ ።)
መጀመሪያ ለመግዛት የሚፈልጉትን መተግበሪያ ይመረጡ፡፡
- ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ ከኦንላይ መግዛት ስለማይችሉ ከሚከተሉት የሚፈልጉትን መተግበሪያዎች ማውረድ ይጠበቅብዎታል፡፡
- መተግበርያውን ካወረዱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲከፍቱት የመጠቀሚያ ኮድ ይጠይቅዎታል፡፡ ይህ ማለት መተግበርያውን ያለገደብ ለመጠቀም ከእኛ የሚገዙት ኮድ ነው፡፡ ይህ ኮድ በስልክዎ የዓለም አቀፍ መለያ ኮድ (IMEI Number) መሠረት የሚፈጠርልዎት ነው፡፡ IMEI ቁጥርዎን መተግበርያው በራሱ ያነብልዎታል ወይም ደግሞ በቀላሉ *#06# በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ለመግዛት የፈለጉትን መተግበርያ ዋጋ በአፕሊኬሽኑ ላይ ከተጠቀሱት በባንኮች ወደሚቀርብዎት በመሄድ ካስገቡ በኋላ ሙሉ ስምዎን ፣ የገዙትን አፕሊኬሽን ስም፣ የስልክዎን IMEI እና የባንኩን ስምና ቅርንጫፍ ወደ እኛ በዚህ ስልክ ቁጥር (+251901008562) ወይም በኢሜይል support@goranda.com ይልካሉ፡፡ ለጊዜው ሁሉንም ሰው በአካል ማስተናገድ ስለማንችል ሙሉ ስምዎንና IMEI ቁጥርዎን በጠቀስነው ስልክ ቁጥር በWhatsApp, IMO, Viber, Telegram መላክ ይችላሉ፡፡
- ሙሉ ስምዎንና ክፍያውን ካረጋገጥን በኋላ በ6 ሰዓታት ውስጥ የመጠቀሚያ ቁልፍዎን እንልክልዎታል፡፡ ይህንን ቁጥር ሲያስገቡ መተግበሪያው መስራት የጀምራል፡፡ያስተውሉ፡- የሚላከው የመጠቀሚያ ቁልፍ ለአንድ ስልክ ብቻ ነው የሚያገለግለው፡፡ ይህም ለሰጡን IMEI ቁጥር ብቻ ማለት ነው፡፡ ለብዙ ስልክ መግዛት ከፈለጉ የፈለጉትን ስልክ IMEI መላክና ክፍያ መፈጸም ይኖርብዎታል፡፡የተላከልዎትን መጠቀምያ ቁልፍ (ኮድ) እንዳይጠፋ በአስተማማኝ ቦታ ያስቀምጡት፡፡
- ስልክዎ ፎርማት ቢደረግ ድጋሜ መተግበርያውን ሲጭኑት ለመክፈት ያስችልዎታል፡፡ ስልክዎ ቢጠፋና ሌላ ስልክ ቢገዙ ወይም ቢቀይሩ አዲስ መክፈቻ ቁልፍ መጠየቅ ይችላሉ፡፡ ይህም እስከ ሁለት ጊዜ ይፈቅዳል። ከዚያ በላይ ግን መጠየቅ አይቻልም። ምክንያቱም በጠፋብኝ ሰበብ ብዙ ሰዎች ሳይጠፋባቸው በነጻ ቁልፎችን ከእኛ ማግኘት ስለሚፈልጉ፡፡ ይህ ችግር ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚኖሩ ብቻ ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ውጪ ለምትኖሩ ከኦንላይን ስለምትግዙ ስልካችሁ ቢጠፋም በአዲሱ ስልክ ኢሜይላችሁን ስታስገቡ ያለምንም ክፍያ ድጋሜ በራሱ ጊዜ መተግበርያችሁ መሥራት ይችላል፡፡
- ከአንድ በላይ መተግበሪያ በአንድ ጊዜ መግዛት ይችላሉ፡፡ አገልግሎቱን ለማግኘት የሁሉንም ስልኮች IMEI መላክ ይጠበቅብዎታል፡፡
- የመጠቀሚያ ቁልፉ ያለምንም ችግር ያለገደብ ለመጠቀም ያስችልዎታል፡፡ መተግበሪያውን በየጊዜው ስለምናዘምነው ያለምንም ክፍያ Update ማድረግ ይችላሉ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በ+251901008562 በደወል ወይም በ support@goranda.com ኢሜይል በመጻፍ እርዳታ ማግኘት ይችላሉ፡፡
እናመሰግናለን፡፡